Where It Began: Launching Bread of Life in Addis Ababa

On October 14, 2026, Bread of Life Ministry held its launch event, the first step of a pilot outreach bringing dignity, relief and hope to unhoused neighbors in Addis Ababa.

10/14/20261 min read

For I was hungry and you gave me food, I was a stranger and you welcomed me... Whatever you did for one of the least of these brothers of mine, you did for me.” (Matthew 25:35-40)

On October 14, 2026 (ጥቅምት 4, 2019 E.C.), we gathered for the launch of Bread of Life Ministry. It was a day of prayer, vision and commitment, and a first step toward serving the people our city too often overlooks.

Bread of Life is a pilot outreach of Ending Well Ministry, operating under Justice For Humanity. It begins in the Piassa and Arada sub-cities of Addis Ababa and serves unhoused adults and mothers with children. Our framework has three phases:

  • Feed: hot meals, hygiene kits, basic first aid and friendship visits, offered with unconditional respect.

  • Form: literacy, trauma-informed care groups, and vocational training in catering, tailoring and repair.

  • Flourish: job placement, microenterprise grants, safe family reunification and dignified elder care.

Our commitments are simple: dignity before dependency, presence before program, and invitation without coercion. We serve with Christ-centered hospitality, honoring every story and every person’s consent.

The launch was only the beginning. Since then we have been out on the streets, sharing meals and the gospel. You can read our most recent outreach in the next post.

"ተርቤ አብልታችሁኛልና፤ እንግዳ ሆኜ ተቀብላችሁኛልና። ከእነዚህ ከታናናሽ ወንድሞቼ ለአንዱ ያደረጋችሁትን ለእኔ እንዳደረጋችሁት ነው።" (ማቴዎስ 25፡35–40)

ጥቅምት 4 ቀን 2019 ዓ.ም (ጥቅምት 14, 2026) የህይወት እንጀራ ሚኒስትሪ የመክፈቻ ፕሮግራም ላይ ተሰብስበን ነበር። ይህ ቀን የጸሎት፣ የራዕይና የቁርጠኝነት ቀን ነበር። ከተማችን ብዙ ጊዜ ችላ ለምትላቸው ወገኖች ለማገልገል የተወሰደ የመጀመሪያ እርምጃም ነው።

የህይወት እንጀራ በ Ending Well Ministry የሚካሄድ፣ በ Justice For Humanity ስር የሚተዳደር የሙከራ የአገልግሎት ፕሮጀክት ነው። አገልግሎቱ የሚጀምረው በአዲስ አበባ ፒያሳና አራዳ ክፍለ ከተሞች ሲሆን፣ መኖሪያ ለሌላቸው አዋቂዎችና ልጆች ላሏቸው እናቶች ያገለግላል። ማዕቀፋችን ሦስት ደረጃዎች አሉት፦

  • ማብላት (Feed)፦ ትኩስ ምግብ፣ የንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁሶች፣ መሠረታዊ ሕክምና እና የወዳጅነት ጉብኝቶች፣ ሁሉም በሙሉ አክብሮት የሚቀርቡ።

  • መቅረጽ (Form)፦ የንባብና የጽሑፍ ትምህርት፣ የስሜት ቁስልን የሚያክሙ የምክር ቡድኖች፣ እንዲሁም በምግብ ዝግጅት፣ በልብስ ስፌትና በጥገና ሙያ ስልጠና።

  • ማበብ (Flourish)፦ የሥራ ቅጥር፣ አነስተኛ ንግድ ለመጀመር የሚሆን ድጋፍ፣ ደህንነቱ የተጠበቀ የቤተሰብ መቀላቀልና የአረጋውያን ክብር ያለው እንክብካቤ።

ቁርጠኝነታችን ቀላል ነው፦ ክብር ከጥገኝነት በፊት፣ መገኘት ከፕሮግራም በፊት፣ ግብዣ ያለ ማስገደድ። የእያንዳንዱን ሰው ታሪክና ፈቃድ እያከበርን በክርስቶስ ፍቅር እናገለግላለን።

የመክፈቻው ፕሮግራም ጅምር ብቻ ነበር። ከዚያ ወዲህ በጎዳና ላይ ወጥተን ምግብና ወንጌልን እያጋራን ነው። የቅርብ ጊዜውን አገልግሎታችንን በቀጣዩ ጽሑፍ ማንበብ ትችላላችሁ።